Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰጠ ማሳሰቢያ
”አለም ፋና የጉዞና የቫዛ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር” ነኝ የሚል የማይታወቅ ህገ ወጥ አካል ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ፈቃድ እንደተሰጠው በማስመሰል ሴቶችና ወጣቶችን በነፃ ወደ ውጭ ሀገር እየላከ እንደሚገኝ በመግለፅ ማንኛውም ስራ መስራት የሚፈልግ በተመቻቸው እድል እንዲጠቀም የሚገልፅ ደብዳቤ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ማረጋገጥ ችለናል።
ሆኖም ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ምስሉ ላይ የተገለፀውን አይነት መጠሪያ ስያሜና የሎጎ ብራንድ የማይጠቀም፣ የውጭ ሀገር ጉዞ አገልግሎት የማይሰጥ፣ የሚሰራጨውም መረጃ ሀሰተኛና ህገ ወጥ ድርጊት መሆኑን እያሳወቅን ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ፣ ራሱን ከወንጀለኞችና ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቅና ምንም ዓይነት ምላሽ መስጠት እንደሌለበት ለማሳሰብ እንወዳለን። የውጭ ጉዞን በተመለከተም ትክክለኛውን መረጃ ከትክክለኛው አገልግሎት ሰጪ ተቋም መውሰድ እንዳለበት በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እንፈልጋለን። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቀጣይም በህገወጥ ድርጊቱ የተሰማሩ አካላትን ከሚመለከታቸው የፍትህ አካላት ጋር በመሆን እንደሚከታተልና ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ እንደሚያደርግ እንገልፃለን።
Please follow and like us:
