በኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ገና የተመራ ልዑክ ቡድን በወጣቶች ተጠቃሚነት ዙሪያ የስራ ጉብኝት ለማካሄድ ኬንያ ናይሮቢ ገብቷል

የልዑክ ቡድኑ በወጣቶች ሁለንናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ዙሪያ ከኬንያ ብሔራዊ ወጣቶች ምክር ቤት ጋር የልምድ ልውውጥ ለማድረግና ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማካሄድ ወደ ስፍራው ማቅናቱ ተገልጿል።

‎‎ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ናይሮቢ የሚገኙት የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ገና ከኬንያ ብሔራዊ የወጣቶች ምክር ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ ግሎሪያ ዋዊራ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። ‎በውይይቱም ሁለቱ ሀገራት ቀደም ሲል ያላቸውን ታሪካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የላቀ እንደነበረ ገልፀዋል። በቀጣይም ይህንኑ ግንኙነት ለማጠናከር ምክር ቤቶቹ በጋራ መስራት እንደሚኖርባቸው የገለጹት ፕሬዝዳንት ፋአድ ገና ይህን ሚና ገቢራዊ ለማድረግ ተቋማዊ ትብብር እና የልምድ ልውውጥ አይተኬ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቷ በበኩላቸው ‎በኬንያ ብሔራዊ የወጣቶች ምክር ቤት የወጣቶች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን በሰፊው አብራርተዋል።

‎‎የስራ ሃላፊዎቹ የሁለቱን አገራት ወጣቶች ሁለተንተናዊ ተሳትፎና አበርክቶ ለማረጋገጥ እንዲሁም አህጉራዊና አለምአቀፋዊ የልማት ግቦችን ለማሳካት በቅንጅት ለመስራት ከስምምነት መድረሳቸውን ምክር ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስፍሯል። ‎ልዑኩ በናይሮቢ ቆይታው በኬንያ የወጣቶች የሰላም እና ደህንነት ብሔራዊ የድርጊት መርሀ-ግብር እና እየተተገበሩ ያሉ ፕሮግራሞችን የሚጎበኙና በጉዳዩ ዙሪያም ውይይት እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።

Please follow and like us: