Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የሀገር ውስጥ አቅም እንዲዳብርና የበጎ ፍቃድ አገልገሎቶች በህክምናው ዘርፍ እንዲስፋፋ ጥሪ ቀረበ
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) የእስራኤል የበጎ ፍቃድ የቀዶ ጥገና ቡድን የሆነውን ኦፕሬሽን ኢትዮጵያ (operation Ethiopia ) መሪ ፕሮፌሰር ሞሪስ ሀርቲስተንን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ሚኒስትሯ እንደገለፁት፥ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የወጣቶች ቁጥር መኖሩን ጠቅሰው እነዚህን ወጣቶች በተለያዩ የስምሪት መስኮች በበጎ ፍቃድ አገልግሎት እንዲሠማሩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚሠራ ጠቁመዋል። የእስራኤል የቀዶ ጥገና ቡድንም ይህን የበጎ ፍቃድ እንቅስቃሴ በተለይም ሀገር ውስጥ ከሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ እንዲሁም የሀገር ውስጥ አቅም እንዲዳብር የበጎ ፍቃድ አገልገሎቶች በህክምናው ዘርፍ እንዲስፋፋ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ጥሪ አቅርበዋል። በተጨማሪም ለአካል ጉዳተኞች የሚያገለግሉ የአካል ድጋፍ መሣሪያዎችን በማሰባሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
የኦፕሬሽን ኢትዮጵያ (operation Ethiopia ) መሪ ፕሮፌሰር ሞሪስ ሀርቲስተንን በበኩላቸው፥ የህክምና ቡድኑ የመጀመሪያ ደረጃ የአይን ህክምና ክብካቤ ከመስጠት እስከ የአይን ቀዶ ጥገና እስከማድረግ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ጠቅሰው ይህንን አገልግሎት በሁሉም አካባቢዎች ለማስፉት መታቀዱንም ገልፀዋል። ከህክምና ቁሳቁሶችና መድሀኒቶች በተጨማሪም ለወጣቶችና ለሴቶች የመጀመሪያ እርዳታ ትምህርትን በስፋት ለመስጠት ቃል የገቡ ሲሆን በቀጣይም ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በቀጣይ አብሮ ለመስራት በሚቻልባቸው ዘርፎች ላይ አጋርነታቸውን ገልፀዋ።
