Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በሰላም ግንባታና ማህበራዊ ትስስርን በማጠናከር ዙሪያ ዘላቂና ቀጣይነት ያለው የወጣቶች ተሳትፎን ማሳደግ የሚያስችል አዲስ ፎረም 2025 ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ውይይት ለሰላም ማህበር ጋር በመተባበር “Youth Building Legacy of Unity and Peaceful Coexisting through meaningful Civics Engagement” በሚል መሪ ቃል ከመጪው ህዳር 19-21ቀን 2018 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ በአድዋ መታሰቢያ አዳራሽ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ይህ የተገለፀው ሚኒስቴሩ ከማህበሩ ጋር በመሆን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን በመወከል መልዕክት ያስተላለፉት አቶ አድነው በዚሁ ወቅት ሚኒስቴሩ የሴቶችና ወጣቶችን ተሳትፎና አቅም ለማሳደግ ከተለያዩ ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር እንደሚሰራ ተናግረዋል። በተለይም ወጣቱ በአሁኑ ሰዓት ከምንጊዜውም በላይ በሰላም ጉዳይ በባለቤትነት መንፈስ መስራት እንዳለበትና መንግስትም ለዚህ ምቹ እየፈጠረ መሆኑን ገልፀዋል። ሰላምን በተመለከተ ወጣቶች ከትናንት በመማር ዛሬን ጠንክሮ በመስራትና ነገን በመፍጠር የራሳቸው አሻራ ማኖር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ውይይት ለሰላም ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወጣት ኢንጂነር ጫላ ኮንፈረንሱ በዋነኝነት በሰላም ግንባታና በማህበራዊ መስተጋብር ዙሪያ ወጣቶችን ዘላቂና ቀጣይነት ያለው ተሳትፎና ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ሲሆን በኮንፈሰንሱ ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ 250 ወጣቶች ይሳተፋሉ ብለዋል። በየአካባቢያቸው ተደማጭና ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች እንዲሁም ግጭት ከሚስተዋልባቸውና ከአርብቶ አደር አካባቢ የተውጣጡ ወጣቶች በኮንፈረንሱ እንደሚሳተፉ አስታውቀዋል።
