የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 54 ሚሊዮን ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ተገለፀ

‎የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን 40ኛውን የዓለም አቀፍ የበጎ ፈቃደኝነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ከKorea International Volunteers organization ጋር በመተባበር “ቅን ልቦች” (We Volunteer) የተሰኘ የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ( Mobile Application) ይፋ አድርጓል፡፡
‎የሞባይል መተግበሪያውን በይፋ የመረቁት ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ባደረጉበት ንግግር፤ በ2017 በጀት ዓመት የክረምት ሦስት ወር ብቻ ከ24 ሚሊዮን በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና ሴቶችን የማሳተፍ ስራ ተሰርቷል፡፡ ‎በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና ሴቶች በተሳተፉበት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትም ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል፡፡ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ 14 የሚሆኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስኮችን ለይቶ እየስራ ነው ያሉት ክብርት ሚንስትሯ፤ የበጎ ፈቃድ አግልግሎት የዜችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለማቃለል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡ ‎የተሰራው የበጎ ፈቃድ አግልግሎት የዜጎችን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባለፈ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ማዳን መቻሉን ገልጸዋል፡፡

‎‎መንግስት ባለፉት ዓመታት እንደ ሀገር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሀገርና የትውልድ ግንባታ ዋነኛ መሰረት መሆኑን አምኖበት ሰፊ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፤ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችም ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡‎የሞባይል መተግበሪያውም የበጎ ፈቃድ አገልገሎትን በማቀላጠፍ፣ በጎ ፈቃደኞችን በማስተሳሰርና በተደራጀ መንገድ በመምራት ረገድ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በበኩላቸው፥ ከቅን ልቦች በተጨማሪ ከ3 ዓመት በፊት volunteerism management Information System /VMIS/ ለምቶ ወደ ስራ መግባቱን አስታውሰው፥ ይህም በአገራዊ የበጎ ፈቃደኝነት ባህል ማሳደግ ጥረት ውስጥ አንድ እርምጃ ወደፊት የሚወሰድ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

Please follow and like us: