22ኛው ዓለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን የማጠቃለያ መርሐግብር “ትውልድን በስነ-ምግባር፣ ተቋምን በአሰራር” በሚል መሪቃል በአድዋ መታሰቢያ አዳራሽ በተለያዩ ዝግጅቶች ተካሂዷል።

በማጠቃለያ መርሐ-ግብሩም የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ እውነቱ አለነ፣ የፌዴራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ክቡር አቶ ሳሙኤል ኡርቃቶ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የፌዴራልና የክልል የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽነሮች እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

‎‎ለሀገራዊ የፀረ ሙስና ትግሉ ጉልህ አስተዋፅዖ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና ተበርክቷል።

Please follow and like us: