‎ሚኒስቴሩ ለአዲስ አበባ የሴቶች ማህበር የሴቶች ማረፊያ ከ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ

ሚኒስቴሩ ዓለም አቀፉ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀን ምክንያት በማድረግ ለአዲስ አበባ የሴቶች ማህበሩ የሴቶች ማረፊያ ከ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደርጓል።

‎ደጋፉን ያስረከቡት የሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሒክማ ከይሬዲን በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፥ አለም አቀፍ ሁነቱን በማስመልከት ጥቃትን መለከላከል ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ፈጠራ ከመስራት ጎን ለጎን ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችና ሕጻናትን መደገፍ እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ማጠናከር የሚያስችል የንቅናቄ እቅድ ተዘጋጅቶ በየደረጃው ሲተገገበር ቆይቷል። ‎የተለያዩ አጋር አካላትን በማስተባበር ጥቃት ለደረሰባቸው ወገኖች የማገገሚያና ጊዜያዊ የመጠለያ አገልግሎት እየሠጡ ያሉ ተቋማት ያሉባቸውን ክፍተት ለመሙላትና ለመደገፍ ሰፊ ጥረት መደረጉንም አስታውቀዋል። ‎በንቅናቄ መርሐግብሩ በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወኑን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ከችግሩ ስፋት አንፃር አሁንም ብዙ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል። ‎አቅም በፈቀደ መጠን በመቀናጀት ተጋግዘንና ተባብረን መስራት ከቻልን የሚጨበጥ ውጤት ማምጣትና የበርካቶችንም ችግር መፍታት እንችላለን ብለዋል።

‎‎የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ በበኩላቸው፥ አስተዳደሩ በተደራጀና በተቀናጀ አግባብ በመንቀሳቀስ ሴቶችና ህፃናትን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ውጤታማ ስራ መሰራቱን ገልፀው ለተደረገው ድጋፍ በማህበሩ ስም አመስግነዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የምግብ፣ የአልባሳትና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ለማህበሩ ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል።
‎

Please follow and like us: