‎3ዐ ሚሊየን ሴቶችን የብሔራዊ ፋይዳ መታወቂያ ባለቤት ለማድረግ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

በዘንድሮ አመት 30 ሚሊየን ሴቶችን የፋይዳ መታወቂያ ባለቤት ለማድረግ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሒክማ ከይረዲን ገለፁ።

‎‎ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የብሔራዊ መታወቂያ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ያለመ የሴቶች ንቅናቄ መካሄድ ተጀምሯል። ‎”ፋይዳ ለሴቶች” ሀገር አቀፍ የንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሒክማ ከይረዲን ባስተላለፉት መልዕክት፥ የመታወቅ መብትን በማረጋገጥ ሴቶች በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መስኮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስቻል ረገድ የፋይዳ መታወቂያ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም ሴቶች ከመታወቅ መብታቸው ተገልለው የመታወቂያ ባለቤት የነበሩት ጥቂቶች ብቻ እንደነበሩ ሚኒስትር ዴኤታዋ አስታውሰው፤ በዚህ ሳቢያ በፍትሕ እና ፋይናንስ ዘርፎች ተጠቃሚ ሳይሆን ቀርተዋል ብለዋል።X‎ዛሬ ላይ ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመሆን በተከናወነው ሥራ ከ30 ሚሊዮን የብሔራዊ መታወቂያ ባለቤቶች ውስጥ 40 በመቶዎቹ ሴቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።

‎ተያዘው ዓመት 30 ሚሊዮን ሴቶች የፋይዳ መታወቂያ ባለቤት ለማድረግ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ክብርት ሒክማ ጠቅሰው ለሀገራዊ ግቡ መሳካት ሁሉም ሃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል። ‎የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና አስተባባሪ ዮዳሔ አርዓያሥላሴ በበኩላቸው፥ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አካታች የመታወቂያ ስርዓት የመዘርጋት አላማን ሰንቆ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ‎የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለሥርዓተ ፆታ እኩልነት መረጋገጥ መሠረት ሆኖ እንደሚያገለግል ገልፀዋል።‎‎የፋይዳ ምዝገባን ተደራሽ ለማድረግ የሴቶች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል።
‎‎ሴቶች ካላቸው ቁጥርና ሀገራዊ ፋይዳ አንፃር የመታወቂያ ባለቤትነት ድርሻቸው ከ50 በመቶ መሻገር እንዳለበት አንስተዋል። ‎በዘንድሮው ዓመት 90 ሚሊዮን ዜጎችን የብሔራዊ መታወቂያ ባለቤት ለማድረግ እየተሠራ እንደሚገኝ በመድረኩ ተገልጿል።

Please follow and like us: