Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ለአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የ 1 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረገ
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አለም አቀፉ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀን ምክንያት በማድረግ ከ 1 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ለአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ድጋፍ አደርጓል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሙና አህመድ በርክክብ መርሐግብሩ ላይ ጥቃት የሰብዓዊ መብት ጥሰት መሆኑን ገልፀዋል። አመለካከቱንም ድርጊቱንም ለማውገዝና ለመከላከል እየተካሄደ ካለው የግንዛቤና የንቅናቄ ስራ ባሻገር የጥቃት ተጎጂ ሴቶችና ሕፃናት ተገቢው ድጋፍ እና እንክብካቤ እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል ብለዋል። ለዚህም ሚኒስቴሩ ከባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመተባበር ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለማዕከሉ የሚውሉ የ 1 ሚሊዮን ብር የሚገመት የህክምና፣ የምግብ፣ የአልባሳትና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ስራ አስኪያጅ አቶ ደጀኔ ገመቹ በበኩላቸው፥ ለተደረገላቸው ድጋፍ በማመስገን በሆስፒታሉ እየተሰጠ ያለውን የአንድ ማእከል አገልግሎት አስጎብኝተዋል።
Please follow and like us:
