የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጉብኝት የሁለቱን ሀገሮች ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ መሆኑ ተገለጸ

ይህ የተገለጸው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር የሆኑትን ክቡር አኒል ኩማር በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው፡፡

ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በውይይቱ እንደገለጹት የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጉብኝትየሁለቱን ሀገሮች ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረና ዲፕሎማሲያዊ ስኬት የተመዘገበበት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ አክለውም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ኢትዮጵያና ህንድ ረጅም እና ጥልቅ የሆነው የእርስ በርስ ግንኙነትና የትብብር ጉዞ ወደ ላቀ ምዕራፍ የሚያሸጋግር መሆኑን ማሳያ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር የሆኑትን ክቡር አኒል ኩማር በበኩላቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደረገው አቀባበልና በነበራቸው ቆይታ እጅግ መደሰታቸውን ገልጸው ወደፊትም የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ትብብርን የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Please follow and like us: