Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር እና የምርምር ስራዎች ባሻገር ለማህበረስብ አገልግሎት ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ ጥሪ ቀረበ
የቀድሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ መምህራንና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ዩኒቨርሲቲው 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዩቤልዩ በዓል አክብሯል።
የዕለቱ የክብር እንግዳና የቀድሞ ተማሪ የነበሩት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለፁት፤ ዩኒቨርሲቲው ሀገራችን የጀመረችውን የለውጥ ጉዞ በአዳዲስ ሃሳቦች፣ ዘመኑ በደረሰባቸው አዳዲስ የትምህርት መስኮች እና የምርምር ስራዎች በማገዝ ለአገራችን የብልፅግና ጉዞ የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል ብለዋል። በተለይም የራስ ገዝነት ጉዞን ጀመረበት ወቅት ዩኒቨርሲቲውን ወደፊት ሊያሻግሩ የሚችሉ የለውጥ ተግባራትን እየከወነ ያለየሀገሪቱ አንጋፋ የትምህርት ተቋም መሆኑን እያስመሰከረ የሚገኝበት ጊዜ ነውሲሉ ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር እና የምርምር ስራዎች ባሻገር በሚቀጥሉት ዓመታት ዩኒቨርሲቲው በማህበረስብ አገልግሎት እና አዳዲስ ፈጠራዎችን በማስፋፋት ለዜጎች የተሻለ ተጠቃሚነት እንዲሰራም ጥሪ አቅርበዋል።
ዩኒቨርሲቲው የጀመራቸው ስራዎች ከሀገሪቱ የለውጥ መንገዶች ጋር በማስተሳሰር ወደ ላቀ ደረጀ እንዲደርስ እገዛ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፈዋል ። የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ከ75 ዓመት በፊት በ50 ተማሪዎች ማስተማርን የጀመረው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ75 ዓመት ጉዞው 300ሺህ ተማሪዎችን ማስመረቁን አስታውሰዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አሻራ በሁሉም ዘርፍ እንደሚታይ ጠቁመው፤ በጥናትና ምርምር ሀገር አሻግረዋል በማስተማር ትውልድ ቀርፅዋል ወደፊትም ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
