Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በ123 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ለጥቃት ተጎጂዎች ሁለገብ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የተሃድሶ ማዕከል ተመረቀ
በአማራ ክልል ጤና ቢሮ እና በአማራ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ትብብር በባሕር ዳር ከተማ የተገነባው የሴቶች የጉዳት ማገገሚያ ማዕከል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተመርቋል።
በምረቃ መርሐ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፥ ባለፉት የለውጥ ዓመታት መንግሥት ለዜጎች ቅድሚያ በመስጠት ሰው ተኮር ሥራዎች ላይ ርብርብ ሲያደረግ ቆይቷል ብለዋል። ከእነዚህ መካከልም የተቋም ግንባታ አንዱ መሆኑን አንስተዋል። ከተባበርን እና በተቋም ሳንታጠር በጋራ ከሠራን ሀገርን እና ሕዝብን የሚጠቅም ለትውልድ የሚሻገር ተግባር ማከናወን እንችላለን ሲሉ ተናግረዋል። የተገነባው የሴቶች ማገሚያ ማዕከል አንዱ የትብብር ማሳያ ነው ብለዋል።
ተቋማት ተገንብተው የሚቆሙ ሳይሆኑ ዘላቂ አገልግሎትን ለማህበረሰቡ በውጤታማነት መሥጠት እንደሚጠበቅባቸውም ጠቁመዋል። ወደ አገልግሎቱ ለማስገባት በሚደረገው ሂደትም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
Please follow and like us:
