‎በሴክተሩ እየተመዘገቡ ያሉ ውጤታማ ተግባራትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በባለቤትነትና በቁርጠኛነት ስሜት መረባረብ እንደሚገባ ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ገለፁ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሴክተር የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ መንፈቅ አመት የስድስት ወር እቅድ አፈፃፀም የግምገማ የጋራ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።
‎‎በመርሐግብሩ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፥ ሴክተሩ በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት የሴቶች፣ ህፃናት፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያንና ሌሎች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ሁለንተናዊ ለመተግበር የታቀዱ ተግባራትን ለማሳካት በየዘርፉ ከፍተኛ ርብርብ መደረጉን ተናግረዋል። ‎ህብረተሰቡን ማዕከል በማድረግ ባለድርሻና አጋር አካላትን በማስተባበር በተሰራው ጠንካራ ስራም በየዘርፉ በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወን መቻሉን ገልፀዋል። ‎

ለአብነትም ባለፉት ስድስት ወራት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ አማራጭ የህፃናት ክብካቤ ስራዎችን በማስፋፋት፣ በሴቶችና ወጣቶች ቁጠባ፣ በተቋማት አካቶ ትግበራ፣ በማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎት ዙሪያ አበረታች ስራዎች መሠራታቸው ተመላክቷል። በቀጣይም በተለይ ከሰላም ግንባታ፣ ከዲጂታል ኢትዮጵያ ግብ፣ ከምርጫ ተሳትፎ፣ ከብሔራዊ ፋይዳ መታወቂያ ተጠቃሚነትና ከሀገራዊ ምክክር አንፃርም ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት ጠቁመዋል።

 

ለዚህም በአሰራር የሚስተዋሉትን ክፍተቶች፣ ከአመለካከት ጋር የተቆራኙትን እንቅፋቶች፣ ከማስፈጸምና ከመፈጸም አቅም ጋር የተያያዙትን ውስንነቶች መፍታትና ለቀጣይ የትግበራ ሂደት ምቹ መደላደል መፍጠር እንደሚገባ ገልፀዋል። ‎በሴክተሩ እየተመዘገቡ ያሉ ውጤታማ ተግባራትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በባለቤትነትና በቁርጠኛነት ስሜት መረባረብ እንደሚገባ ሁሉም እንዲረባረብ በአፅኖት አሳስበዋል።
‎

Please follow and like us: