ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

የገና በዓል የሰው ልጆች ከነበሩበት ዝቅታ የመውጣታቸው ተስፋ የተበሰረበት፤ ከጨለማ ወደ ብርሃን የመምጣታቸው ምዕራፍ የተጀመረበት ተምሳሌታዊ ፋይዳው የገዘፈ ታላቅ በዓል ነው።

‎‎የክርስቶስ ልደት የልዩነትን ግንብ ያፈረሰ፣ የጠብን ግድግዳ የናደ፣ የጥላቻን መጋረጃ የቀደደ፣ የተዋረዱትን ያከበረ፣ የተለያዩትን አንድ ያደረገ፣ የተበተኑትን ያሰበሰበ በዓል ነው፡፡ በዓሉን ስናከብር በመተሳሰብና በመረዳዳት በአብሮነት መንፈስ ካለን በማካፈል፤ የተቸገሩትንና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ወገኖቻችንን ማዕድ በማጋራት በጋራ እንድናከብር ሀገራዊ ጥሪዬን እያቀረብኩ በዓሉ የሰላም የፍቅር የደስታና የአንድነት እንዲሆን እመኛለሁ።
‎
‎ መልካም የገና በዓል!!

Please follow and like us: