Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በኢትዮጵያ የሚደረጉ የሰብዓዊ ድጋፎችና ስትራቴጂያዊ መርሃ ግብሮች ከልማት እቅድና ፕሮግራም ጋር በተናበበ መልኩ መከናወን እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ከወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የኢትዮጲያ ዳይሬክተር ካርመን ቲል የተመራ የልዑካን ቡድን ጋር ከወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በነደፈው አዲስ የ5 ዓመት ስትራቴጂ ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል ፡፡
በውይይቱ ወቅት ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለጹት መንግሥት ለዘላቂ ልማት ትብብሮች ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸው የወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ጣልቃ-ገብነትም ይሄን ውጤታማ እንዲሆን የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራሞችና የማኅበራዊ መዋቅሮችን በተጨማሪነት እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም በኢትዮጵያ የሚደረጉ የሰብዓዊ ድጋፎችና ስትራቴጂያዊ መርሃ ግብሮች ከልማት እቅድና ፕሮግራም ጋር በተናበበ መልኩ መከናወን እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
የወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ዳይሬክተር ካርመን ቲል በበኩላቸው ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በጋራ ለመስራት ከታቀዱ ቁልፍ ነጥቦች መካከል የሕፃናት ጥበቃ ሥርዓትን ማጠናከር፣ ዘላቂ የሆነ የሕፃናት ጥበቃ መዋቅር መገንባት፣ የሥርዓተ-ጾታ ጥቃትን (GBV) መከላከልና ባለፈ ለተጎጂዎች አስፈላጊውን ምላሽ መስጠት፣ የሴቶች ኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና አቅም ግንባታ እንዲሁም ማኅበራዊ ጥበቃ ፕሮግራሞችን ማስፋፋት ላይ በትኩረት ለመስራት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል፡፡
Please follow and like us:
