እንደ ሀገር የተጀመረውን የብልፅግና ጉዞ ለማረጋገጥ የሴቶችን ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አንዱና ዋነኛው እንደሆነ ተጠቆመ።

ይህ የተገለፀው በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቢሾፍቱ ከተማ ጎዲና ወረዳ የሞዴል የልማት ህብረቶች በተጎበኘበት ወቅት ነው።

በጉብኝቱ ወቅት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለፁት ሞዴል የልማት ህብረቶቹ እያደረጉ ያሉትን አንቅስቃሴ አድንቀው እንደ ሀገር የጀመርነውን የብልፅግና ጉዞ ለማረጋገጥ የሴቶች ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አንዱና ዋነኛው እንደሆነ ጠቁመዋል። በዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጀመራቸውን የልማት ህብረቶችን የመደገፍና የማጠናከር ስራውን እንደሚቀጥል ገልፀዋል። በጉብኝቱ ወቅት በሞዴል በልማት ህብረቶቹ የተሰሩ እንስሳት እርባታ ፣ የግብርና ልማት ስራዎች፣ በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶችን ከተባበሩት መንግስታት ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ልዑካንና የክልሉ አመራሮች በተገኙበት ጎብኝተዋል።

Please follow and like us: