የህንድ መንግስት ለሴት ከፍተኛ አመራሮች የአጭር ጊዜ የስልጠና ፕሮግራም በህንድ ሀገር እንዲከታተሉ አዘጋጀ

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አመቻችነት በህንድ መንግስት የአጭር ጊዜ የስልጠና ዕድል ከተሰጣቸው ከፍተኛ ሴት አመራሮች ጋር ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር ከሆኑት ክቡር ሸሪ አኒል ኩማር ራዪ ጋር በመሆን ውይይት አድርገዋል።

‎የስልጠና ዕድሉ ተጠቃሚ የሆኑት ከፍተኛ ሴት አመራሮቹ ከፓርላማ፣ ከኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን፣ ከተለያዩ የሴት አደረጃጀቶች እና ከክልሎች የተውጣጡ ናቸው። ‎በውይይታቸውም የስልጠና ዕድሉ የህንድና የኢትዮጵያን ከፍ ያለውን ስትራቴጂያዊ የሁለትዮሽ ግንኙኝነት ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። በስልጠናው ወቅት ከህንድ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ውይይት የሚደረግ ሲሆን ይህም በሁለቱ ሀገራት ያለውን ግንኙነት የበለጠ እንሚያጠናክርተመላክቷል።

‎በተጨማሪም የሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ የልምድ ልውውጥ የሚደረግበት የመስክ ጉብኝት እንደሚካሄድ ተጠቅሷል። በስልጠና ወቅት በህንድ ፓርላማም በመገኘት ልምድ የሚወሰድበት ፕሮግራም እንደተመቻቸ ተጠቁሟል። በቀጣይም የህንድ መንግስት ለአመራሮች የሚሰጣቸውን የተለያዩ የአጭር ጊዜ ስልጠና እና የረዥም ጊዜ የትምህርት ዕድሎችን ለማመቻቸት የህንድ ኤምባሲ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተገልጿል።

‎

Please follow and like us: