ለ50 ሺህ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል የ2.3 ሚሊዮን ዩሮ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና አምረፍ ሄልዜ አፍሪካ በወጣቶች ዲጂታል አካታችነት እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ እና ለ50 ሺህ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል የ2.3 ሚሊዮን ዩሮ የፕሮጀክት ስምምነት ተፈራርመዋል።

‎ስምምነቱን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የአምረፍ ሄልዝ አፍሪካ ሀገራዊ ፕሮግራም ዳይሬክተር ምስራቅ መኮንን ተፈራርመዋል። ‎ፕሮጀክቱ አዲስ አበባን ጨምሮ በአምስት ክልሎች እንደሚተገበር በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።

‎‎በቀጣይም ፕሮጀክቱን የበለጠ ለማስፋትና ዘላቂነት ባለው መልኩ ለማስቀጠል ተቋማቱ በጋራ ለመስራት ተሰማምተዋል።

Please follow and like us: