በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው እና ከ20 ሺህ በላይ ወጣቶች የተሳተፉበት የ2026 ኢትዮ-አለም አቀፍ የወጣቶች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

‎በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው እና ከ20 ሺህ በላይ ወጣቶች የተሳተፉበት የ2026 ኢትዮ-አለም አቀፍ የወጣቶች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፌስቲቫል “Connecting Mind, Building Futures” ‎በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

‎በፌስቲቫሉ ‎ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ኢትዮጵያ ከ70 በመቶ በላይ ወጣቶች ያሉባት ሀገር እንደመሆኗ በፈጠራ፣ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ረገድ ያላቸውን ክህሎት ለማሳደግ ወጣቶች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል። ‎ፌስቲቫሉ በሀገራችን መካሄድ መጀመሩ ወጣቶችን ከዓለም አቀፍ የዕውቀት ዑደት ጋር የሚያገናኝ ታላቅ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መድረክ ሆኖ ያገለግላል ሲሉ ተናግረዋል።  መድረኩ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ያሉ ወጣቶች ያላቸውን እውቀትና ልምድ የሚለዋወጡበት፣ እርስ በእርስ የሚገናኙበት፣ ያላቸውን የፈጠራ ስራ የሚያሳዩበት፣ ሌሎች የደረሱበትን ደረጃ መመልከት የሚችሉበትን ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።

‎‎የ2030 ዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ በክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ይፋ መሆኑን አስታውሰው ኢንሼቲቩ ይህን እውን ለማድረግ ብሎም ሀገራችን የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ይበልጥ ለማፋጠን ያግዛል ሲሉ ገልፀዋል። ዘመኑ የዲጂታል ቴክኖሎጂ እና አርተፊሻል ኢንተሊጀንስ የተንሰራፋበት ጊዜ በመሆኑ ሚኒስቴሩ በቀጣይም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የትምህርትና የሳይንስ ሰመር ካምፕ በማመቻቸት በዘርፉ ተወዳዳሪ፣ ብቁ የሀገራቸውን ስም የሚያስጠሩና ለሀገራቸው ትልቅ አስተዋፅዖ ማበርከት የሚችሉ ወጣቶችን ለማፍራት በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

‎

Please follow and like us: