Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የዩኔስኮ የሰላም ማዕከል እና ኢድ ኮኔክት ኢትዮጵያ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ማህበራዊ ጥበቃ ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የሶስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የዩኔስኮ የሰላም ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ጋይ ጆከን እና የኢድ ኮኔክት ኢትዮጵያ ቢዝነስ ግሩፕ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሳሙኤል ንጉሴ በስምምነቱ ላይ በመገኘት የመግባቢያ ሰነዱን ፈርመዋል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱ በዋነኝነት ሳይንስና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሴቶችን፣ ወጣቶችን፣ ህፃናትንና ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎችን ፍላጎት ለማሟላት ያለሙ ፕሮጀክቶችን በጋራ ለመንደፍና ለመተግበር ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።
በተጨማሪም የስራ ሃላፊዎቹ በብሔራዊ ደረጃ የሚተገበረውን የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓት እና የማብቃት ስትራቴጂን ከአለም አቀፍ የዲጂታል ምህዳር ጋር በማስተሳሰር ማዘመንና ውጤታማ ማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን ትኩረት ሰጥተው በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።
Please follow and like us:
