‎ኢትዮጵያና ዙምባቤ በወጣቶች አመራር እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

ከስድስተኛው የአፍሪካ ወጣቶች የአመራር ዲፕሎማሲ ጉባኤ (AYLDC)2026 ጎን ለጎን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ

ከዙምባቤ አካባቢ ባለስልጣንና ባህላዊ አመራር ድጋፍ አገልግሎት ምክትል ሚኒስትር ክቡር አልበርት ታዋንዳ፣ ከሐራሬ ከንቲባ እና ሌሎች የልዑካን ቡድናቸው ጋር ትብብርና አጋርነትን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸውም፥ የስራ ሃላፊዎቹ በተለይ በወጣቶች ማብቃትና አመራርነት፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሁም በሰላም ግንባታና በግጭት አፈታት ረገድ የወጣቶችን ሚና ማጎልበት እና የስርዓተ ጾታ እኩልነትን ማረገጋጥ በሚቻልባቸው የትብብር መስኮች ላይ በጋራ ለመስራት በሰፊው መክረዋል።

‎በተጠቀሱት ዘርፎች የበለጠ አጋርነትን ለማጠናከር እና ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ የስራ ሃላፊዎቹ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

Please follow and like us: