‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ፔትኮ ኢትዮጵያ (PETCO Ethiopia) ለችግር ተጋላጭ የሆኑ፣ በአርብቶ አደር አካባቢና በገጠር የሚኖሩ ሴቶችና ወጣቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ፔትኮ ኢትዮጵያ (PETCO Ethiopia) ለችግር ተጋላጭ የሆኑ፣ በከተማና በገጠር እንዲሁም በአርብቶ አደር አካባቢ የሚኖሩ ሴቶችና ወጣቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

‎ስምምነቱን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የፔትኮ ኢትዮጵያ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ምህረት ተክለማሪያም ፈርመዋል። ‎ስምምነቱ በዋነኝነትም በስርዓተ ፆታ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ የግዳጅ ተመላሽ ዜጎችን መልሶ በማቀላቀልና የገጠር ሴቶችን በኢኮኖሚ ማብቃት እንዲሁም በአርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የምግብ ዋስትናና ዘላቂ የኑሮ መተዳደሪያ ላይ ትኩረት ያደረጉ ፕሮግራሞች ማካተታቸው ተጠቁሟል።

ሴቶችና ወጣቶች የራሳቸውን ስራ እንዲፈጥሩ፣ የጀመሯቸውን ስራዎች አጠናክረው እንዲቀጥሉ እና የኢኮኖሚያቸው አቅማቸውን ማሳደግ እንዲችሉ ስምምነቱ የበኩሉን እገዛ እንደሚያደርግ ተገልጿል። ዘላቂነት ያለው የአካባቢ ጥበቃን ብሎም አካታች የኢኮኖሚ ዕድገትን እውን ለማድረግ ጉልህ አስተዋፅዖ የሚያበረክት በመሆኑ ለስምምነቱ ተግባራዊነት በቁርጠኛነት ለመስራት የስራ ሃላፊዎቹ ተስማምተዋል።

Please follow and like us: