Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ሚኒስቴሩ ለ 5 ክልሎች 40 ሚሊየን ብር የሚያወጡ ኮምፒውተሮችን ከነ አክሰሰሪዎቹ አስረከበ።
በትግራይ ፣አማራ ፣አፋር፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ኦሮሚያ ክልሎችና የሚከፋፍል ሲሆን ድጋፉ በክልሎቹና ወረዳዎች ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ተጎጂዎችና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት እንደሚውሉ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በርርክክቡ ወቅት አስታውቀዋል።
በ3R-(መልሶ ማቋቋም) ፕሮጀክት ከአለም ባንክ በተገኘ ገንዘብ ሲሆን ድጋፉ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች ለመደገፍና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራት መካከል መሆኑን ጠቅሰው ይህም የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማቀላጠፍና የተደራጀ የመረጃ አያያዝ ስርዓት መዘርጋት ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል። ለክልሎች የተከፋፈሉት የቴክኖሎጂ ግብዓት ድጋፍ የፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ የድጋፍ አካል መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ ምዕራፎች ሌሎች ድጋፎችም እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
በድጋፍ ከተካተቱት ውስጥ ላፕቶፖች፣ ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ፕሮጀክተሮችን ጨምሮ 321 ልዩ ልዩ ዓይነት ቁሳቁስ ይገኙበታል።
Please follow and like us:
