Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በ“Thamani Africa Awards 2026” የሽልማት መርሃ-ግብር ላይ “በአፍሪካ ምርጥ አፈጻጸም ያሳዩ ሚኒስትር” ተብለው መሸለማቸውን በታላቅ ኩራት እናበስራለን።
የሽልማት ስነ-ስርዓቱ በናይሮቢ፣ ኬንያ በሚገኘው የምስራቅ አፍሪካ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ (Catholic University of Eastern Africa) የተካሄደ ሲሆን፣ ከአህጉሪቱ የተውጣጡ ታዋቂ መሪዎችን፣ ተቋማትን እና ለውጥ አምጪ ግለሰቦችን በአንድነት አሳትፏል።
ይህ እውቅና ኢትዮጵያ ለማህበራዊ ጥበቃ፣ ለሴቶች አቅም ግንባታ፣ ለአካታችነት፣ ለህጻናት ደህንነት እና ማህበረሰብ-ተኮር ልማት ለምታደርገው ቀጣይነት ያለው ጥረት የተሰጠ ትልቅ ክብር ነው። በተጨማሪም ሽልማቱ ለሴቶችና ለተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ዕድሎችን ለመፍጠር እና ሰብአዊ ክብራቸውን ለመጠበቅ በየቀኑ ለሚተጉ ተቋማት፣ ባለሙያዎች፣ የልማት አጋሮች እና ማህበረሰቦች የተሰጠ ምስክርነት ነው። ለክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና በመላው አፍሪካ ትርጉም ላለው ማህበራዊ ለውጥ አስተዋጽኦ ለሚያደርጉ አካላት ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ።

Please follow and like us:
