Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ሚኒስቴሩ የዒድ አል-አረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ300 የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ የማጋራት መርሐግብር አካሄደ
የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመሆን የዒድ አል-አረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ አየር ጤና ሐምዛ መስጊድ በመገኘት ለ300 የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ የማጋራት መርሐግብር አካሂዷል።
በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ክብር አቶ ጌታቸው በዳኔ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት፥ ሚኒስቴሩ የተለያዩ ባለድርሻና አጋር አካላትን በማስተባበር ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ የሚያስችሉ በርካታ በጎ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በዓሉን በመስመልከት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአርዱል-ሀበሻ እና በኢትዮጵያ ከሚገኘው የተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ 300 የህብረተሰብ ክፍሎች የሑድ ሁያ መርሀግብር አዘጋጅቷል ብለዋል፡፡ የማዕድ ማጋት መርሐግብሩ ከጎናችሁ መሆናችንንና ለእናንተ ያለንን ፍቅር ለማሳየት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል።
ለበጎ ስራ መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ለአርዱል-ሀበሻ እና በኢትዮጵያ የሚገኘው የተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ ኤምባሲ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል። እንዲህ አይነቱ መልካም ስራ የህይወት ስንቅ ስለሆነ ወደፊትም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተቀናጀን መሰል ድጋፎችን የምናደረግ ይሆናል ብለዋል፡፡
Please follow and like us:
