የፕሮጀክት ዝግጅት ላይ የሚስተዋሉ ውሱንነት ለመፍታት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።

የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ ዘርፎች የሚስተዋለውን የፕሮጀክት ዝግጅት ውሱንነት ለመፍታት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ለተቋሙ ሰራተኞች አዘጋጅቷል።

‎ስልጠናው የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የተሰጠ ሲሆን በቀጣይ ሚኒስቴሩ በየዘርፉ የሚያከናውናቸው የፕሮጀክት ስራዎች የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ የበኩሉን እገዛ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

Please follow and like us: