‎ሴክተሩ የተጣለበትን ተልዕኮና ኃላፊነት በአግባቡ መወጣትና የዜጎችን የተሻለ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዲቻል ተናቦና ተደጋግፎ መስራት ይገባል ‎- ክቡር አቶ ጌታቸው በዳኔ

የሴቶችና ማህበራዊ ሴክተር የቀጣይ መካከለኛ ዘመን እቅድ ዝግጅት ላይ የፌዴራልና የክልል የቢሮ ኃላፊዎች የተሳተፉበት ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

‎በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሚኒስቴሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ክቡር አቶ ጌታቸው በዳኔ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ባለፉት ሶስት አመታት በወጣቶች፣ በአካቶ ትግበራና በማህበራዊ እንዲሁም በሴቶችና ህፃናት ዘርፍ በተደረገው የጋራ ርብርብ አበረታች ውጤቶች መመዝገብ ችለዋል። ‎በቀጣይም በማህበራዊ ጥበቃና እኩልነት ፖሊሲ ዘርፍ በሴክተር ደረጃም ሆነ እንደ ሀገር የተያዘውን የመካከለኛ ዘመን እቅድ ለማሳካት እና ዜጎችንም የተሻለ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። ሴክተሩ ሰፊ ተልዕኮና ኃላፊነት የተጣለበት መሆኑ ገልፀው፥ ሚናውን በሚገባ እንዲወጣ ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ እስከታች ካለው መዋቅርና የልማት አጋራት ጋር ተናቦና ተደጋግፎ መስራት እንደሚገባ አቶ ጌታቸው በአፅዕኖት አሳስበዋል። ‎የሚኒስቴሩ የስትራቴጂክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ቦጋለ ጣሰው በበኩላቸው፥ የ10 ዓመቱን የመንግስት የልማት እቅድ ማዕከል በማድረግ የሴክተሩ የቀጣይ ሶስት ዓመታት (2019-2021) የመካከለኛ ዘመን የልማት እቅድ እንዲሁም ከዚሁ ስትራቴጂክ እቅድ የተቀዳ የ2019 በጀት አመት እቅድ መዘጋጀቱንና እቅዶቹን የማናበብ ስራ መጀመሩን ገልፀዋል።

‎‎የአካቶ ትግበራን ጨምሮ ከ26 የክልልና የከተማ አስተዳደር የሴክተር ቢሮዎች የተውጣጡ የየዘርፍ እና የእቅድ ክፍል የስራ ሃላፊዎች ከያሉበት አካባቢ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በተገናዘበ መልኩ እቅዱን ካስኬድ እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል። ‎በሴክተር ደረጃ የእቅድና ሪፖርት ወጥነት እንዲኖር ለማስቻል የስራ ሃላፊዎቹ ወደመጡበት አካባቢ ሲመለሱ ታች ያሉ አስፈፃሚ አካላት በተሳተፉበት አግባብ እቅዳቸውን የማናበብ ስራ በተመሳሳይ እንደሚሰሩ ይጠበቃል ብለዋል።
‎

Please follow and like us: