‎‎ተቋማቱ ሴቶችን በኢኮኖሚ ማብቃት፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎትና በክህሎት ሽግግር ላይ ትብብርን ለማጠናከር ተስማሙ

‎በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በቤተ-እስራኤል ማህበረሰብ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና የበጎ አድራጎት ድርጅት እና አክሽን ፎር ሪዝሊያንስ በተሰኘ ሀገር በቀል ተቋም መካከል አጋርነትን ማጠናከርና በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የሶስትዮሽ ውይይት ተካሂዷል።
‎‎ውይይቱ በዋነኝነት ሴቶችን በኢኮኖሚ ማብቃት፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ በእውቀትና ክህሎት ሽግግር፣ በአድቮኬሲና የግንዛቤ ፈጠራ፣ በተግባቦት አቅም ግንባታ ልማት እና በሌሎችም ዘርፎች በትብብር መስራት ላይ ያተኮረ ነው። ‎የተጠቀሱትን ዘርፎች ወደ ተግባር ለማስገባት የሚረዳ የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሰነድ በመፈራረም ለወጤታማነቱ በትብብር እንደሚሰሩ የስራ ሃላፊዎቹ አስታውቀዋል።
Please follow and like us: