የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀንን በማስመልከት የ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በታሪካዊቷ ጅማ ከተማ አከናውናዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ26ኛ፣ በሀገራችን ደግሞ ለ23ኛ ጊዜ በድምቀት እየተከበረ የሚገኘውን ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን አስመልክቶ በታሪካዊቷና በቡና መገኛዋ ጅማ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በማካሄድ ጅማሮውን አድርጓል።
በዚህ “ብዝሀ የወጣቶች እውቀት፤ ለጋራ ትልም!” በሚል መሪ ቃል በተከናወነው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ክብርት ሙና አህመድ፣ የጅማ ከተማ ከንቲባ ክቡር ጠሀ ቀመር ፣ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የክልል የወጣቶች ቢሮ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
Please follow and like us: