ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝቦች በሙሉ፤ እንኳን ለ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር እንዲሁም በየዘርፉ የተጀመሩን የልማት ውጥኖች ከዳር በማድረስ የጋራ ስኬቶችን የምንጎናጸፍበት ዓመት እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ።

‎‎ዘመን ሲለወጥ እውነተኛው መገኛችንና ውበታችን የሚገለጸው አብሮነታችንን ስንጠብቅና ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችንን ስንከባከብ ነው። የዘንድሮው በዓል ሲከበርም ካለን አቅም ፈጥረን ተካፍሎ መብላት፣ የተቸገረን መደገፍ እና እርስ በእርስ መተሳሰብ የዕለት ተዕለት ልማዳችን ሊሆን ይገባል።
‎
‎እጅ ለእጅ ተያይዘን ስንቆም የማያልፍ ፈተና፣ የማንሻገረው ተራራ የለምና በዓሉን ስናከብር የመረዳዳትን እና የመተሳሰብን መንፈስ እንድናስቀድም፤ ፍቅራችንንና አብሮነታችንንም በተግባር በመግለጽ እንዲሆን መልዕክቴን አስተላልፋለሁ፡፡ ‎ባለፉት ዓመታት ያሳየነውን አብሮነት እና ትብብር ይበልጥ በማጠናከር፣ አገራችንን ወደ ላቀ የዕድገት ከፍታ ለማድረስ ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ።
‎
‎ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ
‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር

Please follow and like us: