Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ለኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የምስጋናና እውቅና ፕሮግራም ተካሄደ
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ላለፉት አምስት አመታት ለነበራቸው አጠቃላይ አበርክቶና ድጋፍ የምስጋናና እውቅና ፕሮግራም አካሄደ።

በዕለቱ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአለፉት አምስት ዓመታት ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የተያያዘ ሰፊና ውስብስብ ስራዎችን የሚሰራ በመሆኑ በድጋፍና ክትትሉ ወቅት ከሌሎች ሴክተሮች ይልቅ ጥልቅ እይታን የሚፈልግ መሆኑን በመረዳት ስራውን በቅንጅት ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል። በዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሴቶች፣ ህጻናት፣ የወጣቶች፣ የአረጋውያን፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ከስደት ተመላሾች እንዲሁም ለማህበራዊ ችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መብትና ደህንነት ከማስጠበቅ ባለፈ አካታችነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያከናወናቸውን ሥራዎች አድንቀው፣ በቀጣይም ሥራዎቹን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ሚኒስቴሩ በየዘርፉ ላከናወናቸው ተግባራትና ላስመዘገባቸው ውጤቶች ቋሚ ኮሚቴው ላደረገው ሁለንተናዊ ክትትል፣ ላበረከተው የላቀ አስተዋፅዖ እና ለሰጠው ድጋፍና አመራር ምስጋና አቅርበዋል።
በአምስቱ ዓመታት የትብብር ጉዞ ወቅትም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሀገራዊ አቅሙን ከፍ ባደረጉ የሕግና የአሰራር ማዕቀፎች እንዲሁም የፖሊሲ ሥራዎችን ባከናወነበት ወቅት ቋሚ ኮሚቴ ለነበረው ጠንካራ ቁርጠኝነት እና የትብብር መንፈስ አመስግነዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም የተጀመሩትን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
Please follow and like us:
