Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ሴክተሩ “ሰው ተኮር” እና “አካታች ልማትን” ከግብ ለማድረስ ግንባር ቀደም ሚናውን አጠናክሮ መቀጠል አለበት – ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ
የሚኒስቴሩ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ እና የመጀመሪያው ሩብ ዓመት አፈፃፀም ላይ ለመወያየት ያለመ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የመደመር መንግስት ሀገሪቱ የደረሰችበትን የለውጥ ምዕራፍ ለማፅናትና የብልጽግና ከፍታዋን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሰነቀው ግዙፍ ራዕይ እንዲሳካ ሁላችንም በቁርጠኝነት መስራት ይገባናል ብለዋል።ሴክተሩ “ሰው ተኮር” እና “አካታች ልማትን” ከግብ ለማድረስ ግንባር ቀደም ሚናውን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ማህበረሰባችን ከሴክተሩ የሚጠብቀው ውጤት ሰፊና ፈጣን መሆኑን የተገለጹት ክብርት ሚኒስትሯ፣ የዜጎችን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ፤ በየዘርፉ ያላቸውንም ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከተለመደው አሰራር በመውጣት በአዲስ አስተሳሰብና በባለቤትነት ስሜት መረባረብ እንደሚገባ በአፅዕኖት ገልፀዋል። ለዚህም የተበታተኑ አቅሞችን በማሰባሰብ በቅንጅትና በትብብር መንፈስ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። በአፈፃፀም ሂደት የጎደሉትን ለመሙላት እስከታች የመከታተል፣ የመደገፍና የመመዘንና የተደራጀ ግብረ መልስ የመስጠት ስራ ማጠናከር እንደሚገባ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።
Please follow and like us:
