Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሴክተር የቀጣይ አምስት አመት የመደመር ስትራቴጂክ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሄደ
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮችና የማኔጅመንት አባላት በረቂቅ ደረጃ በተዘጋጀው የሴክተሩ የቀጣይ አምስት አመት ታላቁ የመደመር ስትራቴጂክ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ ወቅት “ሀገራችን ኢትዮጵያ በዕውቀት፣ በአቅም፣ በስራና በሕብረብሔራዊ ወንድማማችነት ላይ የተመሰረተውን “የመደመር” ግዙፍ ስትራቴጂ ተግባራዊ በማድረግ ላይ የምትገኝበት ወሳኝ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ እንደሆነ ተገልጿል። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሴክተር ደግሞ የዚህ መደመር እሳቤ ማዕከል የሆነውን “ሰው ተኮር” እና “አካታችነትን ልማት” ከግብ ለማድረስና እንደሀገር “ማህበራዊ ፍትሕን” እውን ለማድረግ የሚንቀሳቀስ ግንባር ቀደም ተቋም ሊሆን እንደሚገባ ተመላክቷል።
ሰነዱ ታላቁን የመደመር እሳቤ የሚጠይቀው፤ ልዩነቶቻችን አቻችሎ፣ አቅማችን አስተባብሮ፣ በሚቀጥሉት አምስት አመታት ጠንካራ መሠረት የሚጥልና በሂደትም መብትና ደህንነት ተሳትፎና ተጠቃሚነትን፣ አካታችና ማህበራዊ ፍትህን በዘላቂነት በማረጋገጥ ረገድ አቻ የማይገኝለት ውጤት ለማምጣት በሚያስችል መልኩ እንዲዘጋጅ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
Please follow and like us:
