Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
1ሺህ 444ኛውን የኢድአልፈጥር በዓል አስመልክቶ የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ያስተላለፋት መልዕክት።
ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድአልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ጉልህ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሃይማኖታዊ ስርዓቶች መካከል አንዱ በሆነው ታላቁ የሮመዳን ወር የሙስሊሙ ህብረተሰብ ዘወትር ከሚያደርሰው የፆም ፀሎት መርሀ ግብር ጎን ለጎን በተለያዩ ምክንያቶች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ወገኖች በመደገፍና ሌሎችም ከእምነቱ አስተምርሆት የሚጠበቁ በጎ ተግባራትን በማከናወን ማሳለፋቸው ይታወቃል።

ትልቅ በረከት እንደሚያስገኝ በማመን በተለይ በችግር ውስጥ ያሉ ሴቶችን፣ ህፃናትን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ አቅመ ደካማ አረጋውያንን እና ሌሎች ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ህይወት ለመታደግ እንደሀገር በመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላትና በጎ ፈቃደኛ ወገኖች እያደረጉ ያለውን ጥረት በገንዘብ፣ በእውቀት፣ በጉልበትና በጊዜያቸው ጭምር ሲደግፉና ሲያበረታቱ ለነበሩ ሙስሊም እህትና ወንድሞቻችን እናት አባቶቻችን ሁሉ በመንግስት፣ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ በተጠቃሚ ወገኖችና በራሴ ስም ከልብ አመሰግናለሁ።
ጅማሮው ወደፊትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ ለበጎ ስራዎች ሁላችንም ተባባሪ እንድንሆን መልዕክቴን እያስተላለፍኩ በዓሉ የሰላም እንዲሁም መተሳሰባችንና አብሮነታችን ይበልጥ የሚጠናከርበት ብሎም የተቸገሩን ወገኖቻችን የምናስብበትና የምንደገፍበት እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ ።
ኢድ ሙባረክ!
Please follow and like us:
