በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የተመራ ልዑክ በመከናወን ላይ ያሉ የልማት ስራዎችን ለመመልከት ወደ ሀረሪ ክልል አቅንተዋል

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዲሁም የጋምቤላ ክልል በምክትል ርዕሠ መስተዳድር አቶ ታንኳይ ጆክ በመከናወን ላይ ያሉ የልማት ስራዎችን ለመመልከት ወደ ሀረሪ ክልል አቅንተዋል።

የሥራ ኃላፊዎቹ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሮዝል ኡመር፣ የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ፣ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ኡፈ ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም፣ የሀረሪ ጉባኤ አፈ ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። በሀረሪ ክልል በሚኖራቸው ቆይታ በክልሉ ውስጥ በመከናወን ላይ ያሉ የተለያዩ የልማት ስራዎች ተዘዋውረው ይጎበኛሉ።

እንዲሁም ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በሚደረገው የውይይት መድረክ ላይም እንደሚገኙ የሀረሪ ሚዲያ ዘግቧል።

 

Please follow and like us: