የተቋሙ ሰራተኞች በየዘርፉ የተያዙ የልማት እቅዶች እና የተቀመጡ ሀገራዊ አቅጣጫዎች ስኬታማ እንዲሆኑ በላቀ ትጋትና ተነሳሽነት ሊረባረቡ ይገባል

የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ሚኒስቴር ሰራተኞችየተቋሙ ሰራተኞች በየዘርፉ የተያዙ የልማት እቅዶች እና የተቀመጡ ሀገራዊ አቅጣጫዎች ስኬታማ እንዲሆኑ በላቀ ትጋትና ተነሳሽነት ሊረባረቡ እንደሚገባ የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ ገለጹ። የተቋሙ ሰራተኞች በመንግስት ዋና ዋና የማይክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም፣ በ100 ቀናት ስራ አፈፃፀም ግምገማ ወቅት በተሰጡ አቅጣጫዎችና በተቋሙ የ10 ወራት እቅድ አፈፃፀም ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄደዋል።

በመድረኩ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ በተጠቀሱት በአጀንዳዎቹ ዙሪያ ሰፊ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን በተለይ በካቢኔ የተካሄደውን የ100 ቀናት ስራ አፈፃፀም ግምገማ መሠረት በማድረግ የተቀመጡ ተቋማዊና ሀገራዊ አቅጣጫዎችን አብራርተዋል። በገለፃቸውም፥ እንደሀገር ምርታማነትን በሁሉም መስክ ማሳደግና የምግብ ሉአላዊነትን ማረጋገጥ፣ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርምን በጥብቅ ዲሲፕሊን መፈፀም፣ የዲጂታል መታወቂያን አፈፃፀም መደገፍ እንዲሁም የተቋማትን ገፅታ መቀየርና አዳዲስ ሀሳቦችን ማካተት የሚሉት አቅጣጫ ከተሰጠባቸው ጉዳዮች መካከል በዋነኝነት ይገኙበታል ብለዋል።

በተጨማሪም የአረንጓዴ አሻራ ስራዎችን ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እና ዘላቂ ሰላምንና ብልጽግናን ለማረጋገጥ እንዲያስችል በየደረጃው እየተካሄደ ያለው አገራዊ ምክክር ስኬታማ እንዲሆንም አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ትኩረት መሰጠቱንም እስረድተዋል። በተያያዘም በመንግስት ዋና ዋና የማይክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ብሎም በመንግስት ወጪ ገቢ ላይ ዙሪያ ክብርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በዕለቱ የተቋሙ የ10 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትም ቀርቦ በሰራተኛው ውይይት ተካሂዶበታል።

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች እንደሀገርም ሆነ እንደተቋም የተያዙ የልማት እቅዶች እና የተቀመጡ አቅጣጫዎች በሚገባ ተፈጻሚ እንዲሆኑ በየተሰማሩበት መስክ በላቀ ትጋትና ተነሳሽነት መረባረብ እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

 

Please follow and like us: