Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የበጎነትና የአብሮነት አሻራቸውን ለማሳረፍ ዳውሮ ዞን ተርጫ ከተማ ገቡ
(ዳውሮ ታርጫ፣ ሰኔ 30/ 2016 ዓ.ም) በነገው ዕለት በይፋ ለሚጀመረው የዘንድሮ ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር ላይ ለመሳተፍ ብሎም የበጎነትና የአብሮነት አሻራቸውን ለማሳረፍ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ተርጫ ከተማ ገብተዋል።

በዕለቱ የክልሉ ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ጌነት መኩሪያ፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የዞኑና የተርጫ ከተማ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል። የ2016 ዓ.ም ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት “በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባባሪነት በመላ ሀገሪቱ ለ3ኛ ጊዜ እየተካሄደ ይገኛል።
Please follow and like us:
