ኢትዮጵያ 6ተኛውን የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (COMESA) ሴት ስራ ፈጣሪዎች የንግድ ትርዒት ልታዘጋጅ ነው፡

የሴቶች ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጋራ በመሆን ሀያ አንድ የCOMESA አባል ሀገራትን የሚያሳትፍ 6ተኛው የምስራቅና የደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (COMESA) ሴት ስራ ፈጣሪዎች የንግድ ትርዒት እ.ኤ.አ በግንቦት ወር 2025 በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ዛሬ በጽ/ቤታቸው የምስራቅና የደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (COMESA) ስር የሚገኘውን በንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ሴቶች ፌዴሬሽን ተወካዮችን አነጋግረዋል፡፡ ሚንስትሯ እንደገለፁት የንግድ ትርኢቱ ለኢትዮጵያውያን ሴት የስራ ፈጣሪዎች መነቃቃት የሚፈጥርና ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅና የገበያ ትስስር ለመፍጠር እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡

የምስራቅና የደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (COMESA) ስር የሚገኘውን በንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ ሴቶች ፌዴሬሽን ተወካዮች በበኩላቸው ኢትዮጵያ ሰፊ የቆዳ ስፋትና ህዝብ ቁጥር ባለቤት እንደመሆኗ የንግድ ትርኢቱ አዳዲስና ሰፊ የፈጠራ ሃሳቦችን ለመጠቀም እንደሚረዳት ገልጸዋል፡፡ በንግድ ትርኢቱ ላይ ከ 500 በላይ ስራ ፈጣሪ ሴቶች ስራዎቻቸውንና ምርቶቻቸውን ያቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተወካዮቹ ገልፀዋል፡፡

 

Please follow and like us: