Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በ21ኛው ክፍለ ዘመን አፍሪካን ወደፊት ለማራመድ የሚያስፈልገን እነዚህን የብሩህ አዕምሮ ባለቤት ወጣቶችን ይዘን መጓዝ ስንችል ነው ፡፡ – ሁሪያ አሊ
በትላንትናው ዕለት በአድዋ መታሰቢያ ከ48 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ከ4,900 በላይ ባለ ተሰጥኦ ወጣቶችን ያሳተፈው የሀክታወን ውድድር ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡

በዕለቱ ንግግር ያደረጉት በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክብርት ሁሪያ አሊ እንደገለጹት በ21ኛው ክፍለ ዘመን አፍሪካን ወደፊት ለማራመድ የሚያስፈልገን እነዚህን የብሩህ አዕምሮ ባለቤት ወጣቶችን ይዘን መጓዝ ስንችል እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡እነዚህ ወጣቶች ሀገራችን ብሎም አፍሪካ ለሚገጥሟት ማህበራዊ ተግዳሮቶች አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም መልስ መስጠት እንደሚስችል በተግባር ያሣዩበት መድረክ ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስትር ድኤታዋ እንደገለፁት ኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባትና ቴክኖሎጂን ለኢኮኖሚ ልማት ለማዋል የምታደርገው ጥረት አንዱ አካል የሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተጀመረው “5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ” ኢኒሼቲቭ አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ይህ ውጥን 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን በኮዲንግ እና በዲጂታል ክህሎት ለማሰልጠን ያለመ መሆኑን አስታውሰዋል። አክለውም አፍሪካ ሲልከን ቫሊ እነዚህን ወጣቶች ከትምህርት ሂደት ጀምሮ አለምአቀፍ ተቋማት ድረስ ወደስራ ገብተው እራሳቸውን ብሎም አህጉሪቷን እንዲጠቅሙ ላበረከተው አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡

የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድሩ “አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለበጎ ተፅዕኖ” በሚል መሪ ሃሳብ ከግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቷል። በውድድሩ የማጠቃለያ መርሃ ግብር 1ኛ እና 2ኛ የወጡት የቱኒዚያ ወጣቶች 16 ሺህ የአሜሪካን ዶላር 3ኛ የወጡት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ደግሞ 4 ሺህ ዶላር ተሸልመዋል።
