ኢትዮጵያ ያካሄደችውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የቱርክ ኩባንያዎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ።

የኢትዮጵያን መንግስት ወክለው ንግግር ያደረጉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ክብርት ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ ወዳጅነት የገለጹ ሲሆን በቀጣይም ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለመፍጠር ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።

ሚኒስትሯ እንደገለፁት ኢትዮጵያ በቅርቡ ባካሄደችው የኢኮኖሚ ማሻሻያ የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች መፈጠራቸውን ገልፀው በዚህም የቱርክ ኩባንያዎች በአገሪቷ ኢንቨስት እንደሚያደርጉ ጥሪ አስተላልፈዋል።በተጨማሪም፣ ሁለቱ ሀገራት ለህዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት ተጨማሪ የትብብር ዘርፎችን እንደ ማህበራዊ ጥበቃ እና የሴቶች ማጎልበት ፕሮግራሞች ላይም እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

 

Please follow and like us: