የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ከእንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ከእንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ሚኒስትሯ እንደገለፁት ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ ረጅም ታሪክ እና ጥልቅ ግንኙነት እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሯ ጉብኝትም ይሄንን ግንኙነት የበለጠ ያጠናክራል ብለዋል:: በተለይ በማህበራዊ ጥበቃና አካታችነት፣ የሴቶችን መብትና የስርዓተ ፆታ እኩልነት፣ ሴቶች በሰላም ግንባታና ግጭት አፈታት ረገድ ያላቸው አስተዋፅዖ፣ ሴቶችን በኢኮኖሚ ማብቃት እንዲሁም የሴት ልጅ ግርዛትንና ፆታን መሠረት ያደረገ

ጥቃቶችንበመከላከል ዙሪያ እስከአሁን እንደ ሀገር የተሰሩና በመሰራት ላይ ያሉ ሰራዎች ላይ ገለፃ አድርገዋል። የኢንግሊዝ መንግስትና የብሪቲሽ ካውንስል ሴቶች የስራ ፈጣሪዎችና ሴቶችን በኢኮኖሚ ማብቃት ላይ የሚያደርገው እገዛ አንድ አካል በሆነው የሴት የፋሽን ፈጣሪዎች ስራ በዕለቱ ለዕይታ ቀርቧል።

 

Please follow and like us: