የአየርላንድ መንግስት በኢትዮጵያ የጀመራቸውን ስራዎች በትብብርና በቅንጅት ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አረጋገጠ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙትን የአየርላንድ አምባሳደር ኦሊቪያ ሌስሊን ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይቱ ወቅት ሚኒስትሯ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ከነዚህም መካከል ሴቶችን በኢኮኖሚ ለማብቃት እየተደረገ ያለውን ጥረት በሰፊው አብራርተዋል።፡፡ ሚኒስትሯ አክለውም የአየርላንድ መንግስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሚሰራው ስራ ስኬታማነት በትብብርና በቅንጅት ለመስራት መፈለጉን አድንቀው እስካሁንም በማህበራዊ ጥበቃ፣ ሴቶች ማብቃት እና ሌሎች ስራዎች ላይ ለሠራው ስራ እውቅና ሰጥተዋል።

በቀጣይም የአየርላንድ መንግስት በኢትዮጵያ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል ሚኒስትሯ ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ የአየርላንድ አምባሳደር ኦሊቪያ ሌስሊን በበኩላቸው፥ መንግስታቸው የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሚሰራው ስራ በተጨማሪ የስርዓተ-ፆታ እኩልነትን ለማስፈንና ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚያጠናክር ገልፀዋል። ለዚህም ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በትብብርና በቅንጅት ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አምባሳደሯ አረጋግጠዋል፡፡ ስለ ሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች ያሉ ገፆቻችንን ይጎብኙ

 

Please follow and like us: