Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የዘንድሮው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን(ማርች 8) በዓል አከባበር እና ንቅናቄ መርሀ ግብር አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በየዓመቱ የካቲት 29 ወይም ማርች 8 የሚከበረው የሴቶችን ሁለንተናዊ የትግል እንቅስቃሴና ውጤት ለመዘከር፣ ሰፋፊ ንቅናቄዎችን በማካሄድ በሴቶች ዙሪያ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር፣ ወቅታዊ መረጃዎችን ለመስጠት እንዲሁም ሴቶች ላይ የሚሰሩ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ስኬቶችን እንዲያከብሩና ያጋጠሙ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት እንዲረባረቡ ለማስቻል ነው፡፡

በዓሉ የፆታ እኩልነትን በማስፈን ሴቶች ከነበረባቸው ድርብርብ ተጽዕኖ እንዲላቀቁና በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊና በፖለቲካዊ መስኮችም እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማስቻሉም በላይ ቀኑ ሴቶች በህብረተሰቡ ውሰጥ የሚገባቸውን እውቅናና ስፍራ እንዲገኙ ትልቅ መሰረት የጣለ ታላቅ አለም አቀፍ ኩነት ነው፡፡
የዘንድሮውን አለም አቀፍ የሴቶች ቀንም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ “ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል!” በሚል መሪ ቃል በብሔራዊ ደረጃ በተለያዩ መርሐግብሮች እየተከበረ ይገኛል።
እንደሚታወቀው መንግስት በአገራችን የሴቶችን መብት ለማስጠበቅ፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚ ረገድ ያላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የአመራርነትና ውሳኔ ሰጭነት ሚናቸውን ለማሳደግ እየወሰደ ባለው ጠንካራ እርምጃ አበረታች ለውጦች መመዝገብ ችለዋል፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርም በሁሉም ዘርፍ የመጡ ለውጦችን ፈጣንና ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማስቀጠልና የስርዓተ ፆታ እኩልነትን ለማስፈን የሚያስችሉ ስልቶችን በመንደፍና በስራ ላይ በማዋል ለተፈፃሚነቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል፡፡
በዓሉን በዚህ መሪ ቃል ማክበር ያስፈለገው በየዘርፉ የተያዙ ውጥኖች በሚፈለገው ደረጃና ፍጥነት እንዲሳኩ በማስቻል ረገድ የሴቶች ድርሻ የላቀ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቶ ለህብረተሰቡ ለማስገንዘብና ተገቢው ምላሽ እንዲሰጥ ማስቻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡
ይህንኑ ለማሳካት ያመች ዘንድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሁሉም ክልሎችና ከሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት የዘንድሮውን ማርች-8 ከዚህ ቀደም ከነበረው አከባበር በየተለየ መልኩ ሴቶችን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ልዩ ልዩ መርሐግብሮች ለማክበር በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
በዓሉ የሚከበርበት አግባብ፡-
👉በሀገር አቀፍ ደረጃ በዓሉ ከየካቲት 1 እስከ መጋቢት 18 በዋነኛነት የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀትን ከማጠናከርና ሞዴሎችን ከመፍጠር ጎን ለጎን የሴቶችን የቁጠባ ባህል በማሳደግ፣ 15ሺ ሴቶችን የብድር አገልግሎት በማመቻቸት፣ በገቢ ማስገኛ ስራዎች እንዲሰማሩ በማስቻልና የገበያ ትስስር በመፍጠር የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።
👉በማህበራዊ ዘርፍ 4 ሚሊዮን ሴቶች የጡትና የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ እንዲያካሂዱና ጤናቸውን እንዲጠብቁ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።
👉በሌላ በኩል 45 ሺህ ሴቶች በቦንድ ግዢ በነቂስ እየተሳተፉ ለህዳሴው ግድብ ግንባታ እውን መሆን የዜግነት ድርሻቸውን የሚወጡበት አሰራርም ተዘርግቶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በዚህም 22.5 ሚሊየን ብር ግዢ ይፈፀማል ተብሎ ይጠበቃል ።
እንደ ሀገር ለመስራት የታሰቡ ዋና ዋና ስራዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ እነዚህም፡-
👉በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ችግር ምክንያት ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶችና ታዳጊ ሴቶች ለመደገፍ ሀብት በማሰባሰብ ድጋፍ ማድረግ፣
👉ለጥቃተ የተጋለጡ ሴቶችና ታዳጊ ሴቶች የቢዝነስ ክህሎት ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረግ እና ለፆታዊ ጥቃት ተጋላጭ ለሆነው ሴቶች ሁለንተናዊ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፣
👉ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባችው ሴቶች አገልግሎት የሚሰጡ የተቀናጀ የአንድ መስኮት እና የተሃድሶ ማዕከላት ማቋቋምና ማጠናከር፣
👉አዳዲስ የልማት ህብረቶች ማቋቋምና የሴቶች ልማት ህብረቶች ማጠናከር
👉በህብረት ስራ ማህበራት የተደራጁ ሴቶችን ማጠናከር፣
ሴቶች የብድር ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች እንዲሰማሩ ማስቻል፣
👉ሴቶች በተመረጡ ጊዜና ጉልበት ቆጣቢ በሆኑ አዳዲስ ቴክኖሎጂ እንዲጠቀሙ ለማድረግ ግንዛቤ መፍጠር፣
ሴቶች በሌማት ትርፋት ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፣
👉ሴቶች በተለያዩ የስራ እድል መስኮች ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፣
👉የሴቶችን ማህበራዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ከማሳደግ አኳያ ለጤናማ እናትነት፣ ሴቶች በጤና ተቋማት እንዲወልዱ፣ የማህጸን በር ጫፍና የጡት ካንሰርን በሚመለከት ለሴቶች ግንዛቤ መፍጠር፣
👉ታዳጊ ሴቶች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ግንዛቤ መፍጠር፣
👉ሴቶች በሰላም ግንባታና ግጭት አፈታት ዙሪያ ጉልህ ሚና እንዲጫወቱ ማስቻል
በፌደራል እና በክልል ደረጃ ምን ተሰራ?
ክልሎች እቅዳቸውን እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ኦረንቴሽን በመስጠት የጀመሩ ሲሆን የሰላም ኮንፈረንስ ስራዎችን፣ አቅመ ደካሞችን የመጎብኘት እና የመደገፍ ስራዎች፣ የሴቶች ልማት ህብረትን የማቋቋምና የማጠናከር፣ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን በተለይም አቅመ ደካማ ዜጎችን የመንከባከብ እና የሌማት ትሩፋት ስራዎች ተጀምረዋል፡፡
እንዲሁም ሴቶች ጉልበት እና ጊዜ ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀሙ፣ በህብረት ስራ የታቀፉ ሴቶች የብድርና ቁጠባ ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ የማህፀን በር ጫፍ የካንሰር እና የጡት ካንሰር ምርመራ እንዲከናወን፣ የቦንድ ግዢ፣ የደምልገሳ እንዲካሄድ፣ የስራ ዕድል እንዲፈጠር እና ምርቶቻቸውን የማስተዋወቂያና የገበያ ትስስር መፍጠሪያ ፕሮግራም እየተከናወነ ይገኛል፡፡ የጎዳና የስፖርት ሩጫ ለማካሄድም ታቅዷል፡፡
በመሆኑም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለዘንድሮው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓል እንኳን አደረሳችሁ እያለ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የንቅናቄ መርሐግብር ስኬታማነት የፌዴራልና የክልል አስፈፃሚ አካላት በቅንጅት እንዲሰሩና ሴቶችም በባለቤትነት እንዲረባረቡ ጥሪውን ያቀርባል።
