ባለፉት 7 ዓመታት በሴቶችና ማህበራዊ ዘርፍ በርካታ ለውጦች መመዝገባቸው ተገለፀ።

ባለፉት 7 ዓመታት በሴቶችና ማህበራዊ ዘርፍ ፣በህፃናት ፣በወጣቶች፣ በሴቶች፣ በአካል ጉዳተኞች፣ ለችግር ተጋላጭ ዜጎች እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ዘርፎች በርካታ ለውጦች መመዝገባቸውን በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ የሆኑት ክብርት ሁሪያ አሊ የመወያያ ሰነዱን ባቀረቡበት ወቅት ገልፀዋል ።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሀገራዊ ለውጡን 7ኛ ዓመት ” የመጋቢታውያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች! ትላንት ፣ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ ቃል አክብሯል ። በዚሁ ወቅት ባለፉት 7 አመታት እንደ ሀገር የመጡ ለውጦችንና እንደ ሴቶችና ማህበራዊ ከተሠሩ ስራዎች መካከልም ሰው ተኮር የሆኑ ስራዎች፣የሌማት ትሩፋት ስራዎች፣ ዜጋ ተኮር በሆነው የዲፕሎማሲ ስራም ተመላሽ ዜጎችን ወደ ማህበረሰብ የመቀላቀል ስራ፣ ሴቶችን ወደ ውሳኔ ሰጪ ቦታዎች በማምጣትም የሁሉም ዜጋ በእኩልነት ተሳታፊ የሚሆንበት ሁኔታን መንግስት መፍጠሩን ጠቅሰዋል። አክለውም በሀገራችን ያለውን ለውጥ ቀጣይና ዘላቂ ለማድረግ ሁሉም ዜጋ የተፈጠሩትን ምቹ ሁኔታዎችን እንዲሁም ፈተናዎቻችንንም እርስ በርስ በመተጋገዝና ኢትዮጵያዊ ባህሎቻችንን በማዳበር በመፈጠሩ ሁሉም በርብርብ ሊሠራ ይገባል ብለዋል።

በሚኒስቴሩ የሴቶች ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ክብርት ሂክማ ከይረዲን በበኩላቸው እንደገለፁት የኢትዮጵያ የዘመናት ምኞት እውን የሆነበት እና የመጠፋፋት ፖለቲካ በር የተዘጋበት ፣ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የተደረገበት ታሪካዊ ቀን መሆኑንም አውስተው የሀሳብ ልዕልና ቦታ የያዘበት ቀን መሆኑንም ጠቅሰዋል።ከዚህ በተጨማሪም ከተሞችን ለኑሮ የተመቹና እንዲዘምኑ ለማድረግ ታስቦ እየተሠራ ያለው ሥራ ከሀገራችን አልፎ ለአፍሪካ ሞዴል ሥራ መሆን መጀመሩን አያይዘው ጠቅሰዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ የሚኒስቴር መስሪያቤቱ ሰራተኞችና አመራሮች በበኩላቸው ባሳለፍናቸው ዓመታት በሠራናቸው መልካም ሥራዎችና ባጋጠሙን ፈተናዎች ዙሪያ የጋራ መግባባት መፈጠሩን አድንቀዋል።

 

Please follow and like us: