የወጣቶች አመራርነት ሂደትን ለመደገፍ ተለዋዋጩን የአለም ጂኦ ፖለቲካ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ሊሆን እንደሚገባ በሚኒስትሮች የፓናል ውይይት ላይ ተገለፀ።

የፓን አፍሪካ ወጣቶች አመራር ጉባኤ በከሠዓት ውሎው በሚኒስተሮች ደረጃ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ተለዋዋጩን የአለም ጂኦ ፖለቲካ ታሳቢ ያደረገ ወጣት አመራር መፍጠርን ያተኮረ ስርዓት መፍጠር እንደሚገባ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ በሚኒስትሮች መድረክ ላይ ባቀረቡት ፅሁፍ ላይ ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንቱ እንደገለፁት እንደ አህጉር ምቹ ሁኔታዎች ላይ ላንሆን ብንችልም ነገር ግን ከዛ ተሻግረን የተሻለ ለውጦችን መፍጠር እንችላለን ብለዋል።

የፓናል ውይይቱ ተሣታፊዎች፥ ወጣቶችን ማብቃትና ማሣተፍ ከሚለው በዘለለ ወጣቶችን መሠረት ያደረገ የሀገረ መንግስት ግንባታ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል።

በተጨማሪም የአፍሪካውያንን ችግር በራስ ለመፍታት ትውልዶችን ያማከለ ምክክር ማካሄድ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።

በውይይቱ ከ ጋምቢያ፣ ብሩንዲ፣ አልጄሪያ፣ ማሊና ሶማሊያ የተወከሉ ተሣታፊዎች የየሀገራቸውን ልምድ አካፍለዋል።

በተመሳሳይ ከጉባኤው ጎን ለጎን በተካሄደው የጎንዮሽ መድረክ በወጣቶች ሰላምና ደህንነት እንዲሁም የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ ሰነድ ቀርቦ በተሳታፊዎች ጥልቅ ውይይት ተደርጓል።

 

Please follow and like us: