Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው አህጉራዊ ጉባኤ ላይ የተሳተፉ እንግዶች በመዲናይቱ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎበኙ
“የወጣቶች አቅም ለበለጸገች አፍሪካ” በሚል መሪ መልዕክት ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የፓን አፍሪካ ወጣት መሪዎች አህጉራዊ ጉባኤ ላይ የተሳተፉ እንግዶች በመዲናይቱ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ተዟዙረው ጎብኝተዋል።

በልማት ጉብኝት መርሐግብሩ ላይ ከአህጉሪቱ የተውጣጡ ወጣት መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የዲፕሎማት ማኅበረሰብ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በቅርቡ የተመረቀው አዲሱ አለም አቀፍ ኮኖቬንሽን ማዕከል እና ብሔራዊ ቤተመንግስት እንዲሁም የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተሳታፊዎች ከተጎበኙ የልማት ስራዎች መካከል ይገኙበታል። በኢፌዴሪ የቴክኒክና መያ ስልጠና ኢንስትቲዩት እና የምህንድስናና የክህሎት ልህቀት ማዕከል እየተከናወኑ ያሉ የፈጠራ ስራዎችና ተግባር ተኮር የስህጠና ፓኬጆችን ተመልክተዋል።
በተጨማሪም የጉባኤው ተሳታፊዎች የዲጂታል ስታርታፕ ኤግዚቢሽን ጎብኝተዋል። ለክቡራን እንግዶች እንጦጦ ፓርክ በሚገኘው የኩሪፍቱ ሪዞርት የክብር የምሳ ግብዣ ተካሂዷል። የመርሐግብሩ ተሳታፊዎች በተመለከቱት የልማት ስራዎች፣ በተደረገላቸው አቀባበልና መስተንግዶ መደሰታቸውን በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል። ዛሬን ጨምሮ ላለፉት ሁለት ቀናት በተካሄደው ጉባኤ በተለያዩ ዘርፎች የወጣት አፍሪካውያን መሪዎችን አቅም የሚያጎለብቱ ጥልቅ ውይይቶች ሲደረጉ መቆየቱ ይታወቃል።
Please follow and like us:
