የአህጉራዊ ጉባኤው ተሳታፊ ወጣቶች የሰንሻይን ፊላትሮፒ ፋውንዴሽን የአረጋውያን መጦሪያና መንከባከቢያ ማዕከል ጎበኙ

የአህጉራዊ ጉባኤው ተሳታፊ ወጣቶች የሰንሻይን ፊላትሮፒ ፋውንዴሽን የአረጋውያን መጦሪያና መንከባከቢያ ማዕከል እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

ወጣቶቹ በማዕከሉ ለሚገኙ አረጋውያን እየተሠጠ ያለውን የተቀናጀና ሁለገብ የድጋፍና እንክብካቤ አገልግሎት ተመልክተዋል። ወጣቶቹ በዚሁ ጊዜ፥ በማዕከሉ ለሚገኙ አረጋውያን ልዩ ልዩ ድጋፍ አድርገዋል። ሰንሻይን ኮንስትራክሸን ኢንቨስትመንት ግሩፕ በተለያየ ምክንያት ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ አረጋውያንን ከወቀደቁበት በማንሳት በጊዜያዊነትና በዘላቂነት ለመደገፍ እና ተጠቃሚ ለማደረግ እያከናወናቸው ያሉትን ተግባራትን አደንቀዋል።መሠል የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ የተሠማሩ ተቋማትን በተደራጀ አግባብ መደገፍና ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

ለዚህም ሁሉም አቅም የፈቀደውን እገዛ ማድረግ እንዳለበት በጉብኝቱ ወቅት ገልፀዋል።አረጋውያኑ ወጣቶቹ በመጎብኘታቸውና በአቅማቸው ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል።

Please follow and like us: