Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በየዘርፉ የተሻለ ለውጥ ለማምጣትና ዜጎችንም የላቀ ተጠቃሚ ለማድረግ ሁሉም በየተሰማራበት መስክ ሊረባረብ ይገባል
የ2017 ሀገራዊና የሴክተር የ9 ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የሚኒስቴሩ አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

በመድረኩ፤ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ባለፉት ዘጠኝ ወራት እንደሀገርም ሆነ እንደተቋም በየዘርፉ ትልቅ ውጤት መመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል። የተመዘገበው ስኬት የሁሉም አስፈፃሚ አካል ድምር ውጤት መሆኑን ጠቅሰዋል። ቀጣይም በየዘርፉ ለውጥ ለማምጣትና በሴክተሩ ተደራሽ የሆኑትን የህብረተሰብ ክፍሎች የተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ ሰፊ ርብርብ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል።

ለዚህም እንደመንግስት አገልጋይ ሁሉም ሚናውን በውል በመገንዘብና የተሰጡትንም ተልዕኮዎች ከሀገራዊ እቅዱ ጋር በማስተሳሰር በላቀ ትጋት መስራት፣ የመንግስትን ጥረት መደገፍና ለስኬታማነቱ መተባበር አለበት ብለዋል። እንደሴክተር የሚስተዋሉትን ችግሮች መፍታት ይገባል ያሉት ክብርት ሚኒስትሯ በቀጣይ በተለይ የመረጃ ችግርን ለመፍታት የሚያስችል ውጤታማ የዲጂታል ስርዓት ለመዘርጋት በቅንጅት ይሰራል ብለዋል። በተጨማሪም ለስራ ዕድል ፈጠራ፣ ለገጠር ልማት ስራዎች እንዲሁም ለሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ተግባራዊነትና ስኬታማነት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

በመድረኩ የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሙና አህመድ በ2017 ባለፉት ዘጠኝ ወራት አለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያ ለኢትዮጵያ ያለው አንድምታ ብሎም እንደሀገር መንግስት የወሰዳቸው የማክሮ ኢኮኖሚና ሀገር በቀል የሪፎርም ማሻሻያ አፈፃፀሞችና የተገኙ ውጤቶች ምንድናቸው የሚሉትን በንፅፅር አብራርተዋል። በሌላ በኩል የስትራቴጂክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ማዕረግ መኮንን በበኩላቸው በተቋሙ በሴቶችና ህፃናት፣ በወጣቶች እንዲሁም በማህበራዊ ጥበቃ ዘርፍ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን አቅርበዋል።
