ሚኒስቴሩ በዓሉን አስመልክቶ ለሰላም የህፃናት መንደር የ5 መቶ ሺህ ብር ድጋፍና ማዕድ አጋራ።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለት ለሰላም የህፃናት መንደር የ5 መቶ ሺህ ብር ድጋፍና ማዕድ ማጋራት አከናውኗል።

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያዊ የመደጋገፍና የመተሳሰብ እሴት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም የበኩሉን ጥረት ማድረግ እንዳለበት ገልፀዋል። ሁሉም ማህበረሰብ በዓሉን ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውንና የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትና አብሮ በማሳለፍ ሁላችንም የድርሻችንን አስተዋጽኦ በማድረግ በዓሉን በጋራ እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል ። የሰላም ህፃናት መንደር መስራች ፀሀይ ሮሺሊ በበኩላቸው ሚኒስቴር መ/ቤቱ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው ሌሎችም ተመሳሳይ እገዛና ድጋፍ እንዲያደረጉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ሰላም የህፃናት መንደር እ ኤ አ በ1986 ጀምሮ ወላጅ የሌላቸውንና ለችግር የተጋለጡ ህፃናትን፣ወጣቶችን፣ሴቶችንና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች አስፈላጊውን የምግብ የመጠለያና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች በማሟላት እየሰራ ይገኛል።

 

Please follow and like us: