Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን የአፍሪካ የሰዎችና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር እና የአፍሪካ የሴቶች መብቶች ፕሮተኮል ወቅታዊ የሰብአዊ መብቶች አፈጻፀም ሪፖርቶችን ማቅረብ ጀመረ
በፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን በአፍሪካ የሰዎችና ህዝቦች መብቶች ቻርተር (ባንጁል ቻርተር) ከ7ኛ እሰከ 10ኛ የተጠቃለለ ወቅታዊ የኢትዮጵያ አፈጻፀም እና በአፍሪካ የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል) መነሻ ወቅታዊ አፈጻፀም ላይ ሪፖ
ርቶችን ማቅረብ ጀመረ።
ስብሰባው በጋምቢያ ባንጁል በሚገኘው የአፍሪካ የሰዎች እና ህዝቦች መብቶች ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት እየተካሄደ ነው። በስብሰባው ወቅት የልዑክ ቡድኑ አባላት ኢትዮጵያ በሪፖርት ዘመኑ በአፍሪካ የሰብአዊና ህዝቦች መብቶች ቻርተር እና በማፑቶ ፕሮቶኮል መሰረት ያሉባትን ግዴታዎች ለመወጣት እና የሰብአዊ መብቶችን ከማስፋፋትና ከማስጠበቅ አንጻር የተወሰዱ የፖሊሲ፣ የህግ እና ተቋማዊ እርምጃዎችን የሚመለከቱ ለውጦችን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
በኮሚሽኑ መርሃ ግብር መሰረት፣ የቀረቡ ሪፖርቶችን ተከትሎ ከኮሚሽነሮች ለተነሱ ጥያቄዎች ሀገራችን ኢትዮጵያ በልዑክ ቡድኑ አማካኝነት ምላሾችን ትሰጣለች ተብሎ ይጠበቃል። መድረኩ ኢትዮጵያ በባንጁል ቻርተር እና በማፑቶ ፕሮቶኮል ስምምነቶች መሰረት በአገሪቱ የሰብዓዊ መብቶችን እና የፆታ እኩልነትን ለማጎልበት ያላትን ቁርጠኝነት የምታሳይበት መድረክ ከስፍራው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
Please follow and like us:
